በትብብር መማር አንብቦ በመረዳት ችሎታና ፍላጎት ላይ ያለው ሚና(በ11ኛ ክፍል የፋሲለደስ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተተኳሪነት)አማራ ክልል፡ ኢትዮጵያ

Authors

  • ፋሲካ ውበቱ
  • አገኘሁ ተስፋ

Keywords:

በትብብር መማር, አንብቦ መረዳት, ፍላጎት

Abstract

የጥናቱ ዋና ዓላማ በትብብር መማር አንብቦ በመረዳት ችሎታና ፍላጎት ላይ ያለውን ሚና መመርመር ነው። የጥናቱ ንድፍ ባለሁለት ቡድን ፍተነታዊ ነው። የጥናቱ ተሳታፊዎች በሰሜን ጎንደር ዞን በጎንደር ከተማ በፋሲለደስ መሰናዶ ትምህርት ቤት በ2009 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙት 1201 ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጪ ንሞና የተመረጡ የ11ኛ K እና የ11ኛ B ክፍል ተማሪዎች ናቸው። ከእነሱም በፈተናና በጽሑፍ መጠይቅ አማካይነት የጥናቱ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች በነጻ ናሙና ቲ-ቴስት (Independent Samples t-test)ተተንትነዋል። በውጤት ትንተናው መሠረትም የሙከራው ቡድን ድኅረትምህርት አንብቦ የመረዳት ፈተና አማካይ ውጤት ከቁጥጥሩ ቡድን አንብቦ የመረዳት ፈተና አማካይ ውጤት በልጦ ጉልህ ልዩነት (p = 0.0428) አሳይቷል። በተመሳሳይ መልኩ የሙከራው ቡድን የድኅረትምህርት የማንበብ ፍላጎት የጽሑፍ መጠይቅ አማካይ ውጤት ከቁጥጥሩ ቡድን የማንበብ ፍላጎት የጽሑፍ መጠይቅ አማካይ ውጤት በልጦ ጉልህ ልዩነት (p = 0.0206) አሳይቷል፡፡ ከዚህም በመነሳት በትብብር መማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ፍላጎት ለማሳደግ ከተለመደው ግላዊ የመማር ምርጫ የበለጠ አስተዋጽኦ አለው ከሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሷል። በጥናቱ ውጤት መሰረትም በትብብር መማር የተማሪዎችን የማንበብ ችሎታና የማንበብ ፍላጎት ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑ በመፍትሄነት ተጠቁሟል።

Downloads

Published

2020-12-16